የመኸር እርሻ አፈጻጸምን ለመገምገምና የበጋ መስኖ ዝግጅትን ለማጠናከር የመስክ ምልከታ ተካሄደ
ሀዋሳ፣ጥቅምት 17/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)የመኸር እርሻ አፈጻጸምን ለመገምገምና የበጋ መስኖ ዝግጅትን ለማጠናከር የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
በደቡባዊ ሲዳማ ዞን የመኸር እርሻ አፈጻጸምና የበጋ መስኖ ዝግጅት በተመለከተ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሱፋው ጎኔሶ የመሩት ቡድን በደቡባዊ ሲዳማ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በመገኘት የመኸር ወቅት የእርሻ ሥራዎችን የመስክ ምልከታ አካሂዷል።
የመስክ ምልከታው ዋና ዓላማ በመኸር እርሻ ወቅት የተለያዩ የግብርና ግብዓቶች አጠቃቀምን፣ የሰብል ልማት ሁኔታን፣ የበሽታና የአረም ቁጥጥር ሥራዎች አፈጻጸምን በተግባር በመገምገም የተሻለ የግብርና ሥራ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለመለየት ነው።
በዚህ ወቅት የቢሮው ኃላፊ አቶ አሱፋው ጎኔሶ እንደገለጹት፣ የመስክ ምልከታው በግብርናው ዘርፍ የተያዙ ዕቅዶች በተግባር እየተፈጸሙ ያሉበትን ሁኔታ ለመረዳት፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማጠናከር፣ ያሉ ክፍተቶችን ለመለየትና በወቅቱ አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ወሳኝ ነው።
በተለይም የግብርና ግብዓቶችን በትክክለኛ ጊዜና በአግባቡ መጠቀም፣ የሰብል በሽታና አረም ቁጥጥርን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን የምርትና ምርታማነት ዕድገትን ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።
ከመኸር እርሻ አፈጻጸም ግምገማ በተጨማሪ፣ የበጋ መስኖ ልማትን በዕቅዱ መሠረት ለማስፈጸም የተደረጉ ዝግጅቶችም ተመልክተዋል። በዚህም የመሬት ዝግጅት ሁኔታ፣ ለመስኖ ልማት ተስማሚ የሆኑ መሬቶችን የመለየት ሥራ፣ የመስኖ አውታሮችን የመለየትና የማዘጋጀት ሂደት እንዲሁም የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት አፈጻጸም ተገምግሟል።
የበጋ መስኖ ልማት ዝግጅትን በወቅቱና በተቀናጀ ሁኔታ ማከናወን የመሬትና የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም፣ የሰብል ምርትን ለማሳደግ፣ የአርሶ አደሩን የገቢ ምንጭ ለማስፋትና የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደምያበረክት አቶ አሱፋው ገልጸዋል።
የመስክ ምልከታው በመኸር እርሻ ወቅት የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም ቀሪ ሥራዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን፣ የግብርና ሥራዎችን በቅንጅት ለማስፈጸምና ለበጋ መስኖ ልማት የተደረጉ ዝግጅቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ጠቃሚ የክትትልና የግምገማ ሂደት ነው።
#Latino Irsha Maatete Jireenyira
# የለማ እርሻ ለቤተሰብ ብልፅግና
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለቢሮአችን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
📌ፌስቡክ ፦https://www.facebook.com/sidamaregionaagriculture
*
📌ቴሌግራም :-https://t.me/+5on3EIZtHzxmMzNk
📌ዩቲዩብ:-https://
www.youtube.com/@SidamaBOACommunicationDirector
📌 Tiktok:-
tiktok.com/@sidamaboacommndirectoret
ዜና
News / 27 ኦክቶበር 2026
ሀዋሳ፣ጥቅምት 17/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)የመኸር እርሻ አፈጻጸምን ለመገምገምና የበጋ መስኖ ዝግጅትን ለማጠናከር የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
