CALM
01የCALM P for R ፕሮግራም አጠቃላይ እይታ
CALM P for R ፕሮግራም የተፋሰስ ህብረት ስራ ማህበር መሰረት በማድረግና ሰፊው ህዝብ በማንቀሳቀስ የተሳትፎአዊ ማህበረሰብ እቅድ እና ትግበራ የሚሰራ ፕሮግራም ነዉ፡፡
ይህ ፕሮግራም በክልላችን 2012ዓ.ም ጀምሮ በ366 ተፋሰስ ህ/ስራ ማህበር ላይ በ31 ወረዳዎች፤ 343 ቀበሌ ዉስጥ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የፕሮግራሙ ሽፋን
- 366 ተፋሰሶች
- 31 ወረዳዎች
- 343 ቀበሌዎች
- 193,538.82 ሄ/ር
- ወንድ ተሳታፊዎች: 128,202 አባላት
- ሴት ተሳታፊዎች: 49,352 አባላት
- ጠቅላላ ተሳታፊዎች: 177,554 አባላት
02የCALM-NRM ዋና ዋና ተግባራት
- አካላዊ የአፈር እና የውሃ ጥበቃ ስራዎች
- የጎርፍ መቆጣጠሪያ እና የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይዎች
- ዘላቂ የመሬትና ደን አስተዳደር ጥበቃ ስራዎች
- የአግሮደን ልማት፣ የግጦሽ ልማት እና የደን ልማት
- የቦረቦር ማልማት ማገገሚያ ልምዶች
- የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ስራዎች
03የመጀመሪያ ክፍያ አመላካች (DLI-1)
መጀመሪያው የክፍያ አመላካች DLI_1 ፕሮግራሙ በሁሉም ወረዳዎች የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት አስፈላጊ የሆኑ ባለድርሻ አካላቶችን በማወያየት አዋጆች እና አለምአቀፍ ስምምነቶች ደንቦችና መመሪያዎች የማስረጽ ስራ ተስርቷል።
04የሁለተኛ ክፍያ አመላካች (DLI-2)
የማህበራት ሰነድ ዝግጅት
- የስራ አመራር ኮሚቴዎች ምርጫ
- የ5 ዓመትና የ1 ዓመት እቅድ ዝግጅት
- የይሁንታ ሰርትፍኬት ማዘጋጀት
የማህበሩ ሰነዶች
- የማህበሩ ብሮ
- የተለያዩ መዛግብቶች
- የማህበሩ ማህተም
- የገቢና የወጪ ሰነዶች
05የሶስተኛ ክፍያ አመላካች (DLI-3)
በ366 ተፋሰስ ህ/ስራ ልማት ማህበራት ውስጥ 133,601 ሄክታር ለማልማት ታቅዶ 123,036.4 ሄክታር (93%) ሊከናወን ችሏል።
- ጠረጴዛማ እርከን
- ደልዳላ የአፈር ካብ
- ፋንያጁ
- የውሃ ማሰባሰቢያ ቴክኖሎጂዎች
- ጥምር ደን ልማት
- የፍራፍሬ ችግኝ ማሰራጨት
06የአባላቱ የኑሮ ማሻሻያና የገቢ ምንጭ የስራ መስክ
የስራ መስክ ተጠቃሚዎች
- እንስሳት ማድለብ: 1817
- ማሞከት: 4517
- ንብ ማነብ: 2219
- ዶሮ እርባታ: 17579
- ሰብል ማምረት: 3946
- ቨርም ኮሚፖስት: 660
- ችግኝ ዝግጅት: 137
- ንግድ: 424 ቡድኖች
ተሳታፊዎች
- 23,283 ወንድ
- 8,016 ሴት
- 31,299 ጠቅላላ
07የተመደበ በጀት
በCALM-NRM ፕሮግራም 929,535,579.90 ብር በጀት በመመደብ ለተጠቃሚዎች እየተደረሰ ይገኛል።
08የአቅም ግንባታ ስልጠና
በ6 ዓመታት ውስጥ 320,200 ባለድርሻ አካላት በድግግሞሽ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።