‎የREDD+ Investment ፕሮግራምን ውጤታማነት ለማሳደግና የደን ሀብትን ለመጠበቅ የጋራ አቅጣጫ ተቀመጠ
‎
‎ሀዋሳ፣ ጥቅምት 02/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)የREDD+ Investment ፕሮግራምን ውጤታማነት ለማሳደግና የደን ሀብትን ለመጠበቅ የጋራ አቅጣጫ ተቀመጠ።
‎
‎የREDD+ Investment ፕሮግራም አፈጻጸምን በመገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከርና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
‎
‎ፕሮግራሙ በ2010 ዓ.ም. በአሮሬሳ ወረዳ የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሆኮ፣ ጫቤ-ጋምቤልቱ እና ዳኤላ ወረዳዎች በደን ልማትና ጥበቃ ሥራዎች ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
‎
‎የውይይት መድረኩን የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሱፋው ጎኔሶ የመሩት ሲሆን፣ በፕሮግራሙ የታቀፉ ወረዳዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
‎
‎ደንን መጠበቅ የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ የአካባቢ ሚዛንን ለማስጠበቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለ አካባቢ ለማውረስ ወሳኝ ሚና እንደለው የቢሮ ኃላፊ አቶ አሱፋው ገልጸዋል።
‎
‎በመድረኩም የፕሮግራሙ አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግሞ፣ የታዩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ተለይተዋል።
‎
‎በቀጣይም የታዩ ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት፣ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከርና የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የቀጣይ ሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
‎
‎በተለይም የተቋማትን ቅንጅት ማጠናከር፣ የአመራርና የባለሙያዎችን ኃላፊነት ማሳደግ እና በጋራ በመሥራት የደን ሀብትን ለዘላቂ ልማት ማዋል እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ አቅጣጫ አስቀምጧል።
‎
‎#Latino Irsha Maatete Jireenyira
‎# የለማ እርሻ ለቤተሰብ ብልፅግና
‎
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለቢሮአችን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
‎
‎ 📌ፌስቡክ ፦https://www.facebook.com/sidamaregionaagriculture
‎*
‎📌ቴሌግራም :-https://t.me/+5on3EIZtHzxmMzNk
‎
‎📌ዩቲዩብ:-https://
‎www.youtube.com/@SidamaBOACommunicationDirector
‎
‎ 📌 Tiktok:-
‎tiktok.com/@sidamaboacommndirectoret
‎