የREDD+ Investment ፕሮግራምን ውጤታማነት ለማሳደግና የደን ሀብትን ለመጠበቅ የጋራ አቅጣጫ ተቀመጠ
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 02/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)የREDD+ Investment ፕሮግራምን ውጤታማነት ለማሳደግና የደን ሀብትን ለመጠበቅ የጋራ አቅጣጫ ተቀመጠ።
የREDD+ Investment ፕሮግራም አፈጻጸምን በመገምገም፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከርና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።
ፕሮግራሙ በ2010 ዓ.ም. በአሮሬሳ ወረዳ የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሆኮ፣ ጫቤ-ጋምቤልቱ እና ዳኤላ ወረዳዎች በደን ልማትና ጥበቃ ሥራዎች ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
የውይይት መድረኩን የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሱፋው ጎኔሶ የመሩት ሲሆን፣ በፕሮግራሙ የታቀፉ ወረዳዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ደንን መጠበቅ የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ የአካባቢ ሚዛንን ለማስጠበቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለ አካባቢ ለማውረስ ወሳኝ ሚና እንደለው የቢሮ ኃላፊ አቶ አሱፋው ገልጸዋል።
በመድረኩም የፕሮግራሙ አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግሞ፣ የታዩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ተለይተዋል።
በቀጣይም የታዩ ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት፣ የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከርና የፕሮግራሙን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የቀጣይ ሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በተለይም የተቋማትን ቅንጅት ማጠናከር፣ የአመራርና የባለሙያዎችን ኃላፊነት ማሳደግ እና በጋራ በመሥራት የደን ሀብትን ለዘላቂ ልማት ማዋል እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊ አቅጣጫ አስቀምጧል።
#Latino Irsha Maatete Jireenyira
# የለማ እርሻ ለቤተሰብ ብልፅግና
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለቢሮአችን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇
📌ፌስቡክ ፦https://www.facebook.com/sidamaregionaagriculture
*
📌ቴሌግራም :-https://t.me/+5on3EIZtHzxmMzNk
📌ዩቲዩብ:-https://
www.youtube.com/@SidamaBOACommunicationDirector
📌 Tiktok:-
tiktok.com/@sidamaboacommndirectoret
Hawalle
News / 27/10/2026
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 02/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)የREDD+ Investment ፕሮግራምን ውጤታማነት ለማሳደግና የደን ሀብትን ለመጠበቅ የጋራ አቅጣጫ ተቀመጠ።
