ሀዋሳ፣ ጥቅምት 07/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)በሄክታር እስከ 32 ኩንታል ምርት የሚሰጠው አዲሱ የቦሎቄ ምርጥ ዝርያ ወደ ክልሉ ወረዳዎች ለማስፋት የዝርያ ማባዛት ሥራ እየተከናወነ ነው።
የሲዳማ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያዘጋጀውን “ቀይ ቡሬ” የተሰኘውን አዲስ የቦሎቄ ምርጥ ዝርያ በክልሉ ወረዳዎች ለማስፋት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ።
በዚህ ዓላማ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን፣ ቢላቴ ዙሪያ ወረዳ በ12 አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በ15 ሄክታር መሬት የተዘራውን የቀይ ቡሬ ቦሎቄ መሠረታዊ ዘር (Basic Seed) ለማስፋት ያለመ የአርሶ አደር መስክ ቀን መርሐ ግብር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።
ዝሪያውን ከዚህ በፊት የተገኙ ግኝቶች ለየት የሚያደርገው ከፍተኛ ምርታማነት ፣በሽታን የመቋቋም አቅም የተሻለ፣ የንጥረ ነገር ይዘት እና የገበያ ተፈላጊነቱ የአርሶ አደሮችን የገቢ አቅም ለማሳደግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ተገልጸዋል።
ዜና
News / 25 ኦክቶበር 2026
ሀዋሳ፣ ጥቅምት 07/2019(የቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ዳይሬክቶሬት)በሄክታር እስከ 32 ኩንታል ምርት የሚሰጠው አዲሱ የቦሎቄ ምርጥ ዝርያ ወደ ክልሉ ወረዳዎች ለማስፋት የዝርያ ማባዛት ሥራ እየተከናወነ ነው። የሲዳማ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በምርምር ያዘጋጀውን “ቀይ ቡሬ” የተሰኘውን አዲስ የቦሎቄ ምርጥ ዝ…
