የባለስልጣኑ አስፈላጊነት
በክልሉ መንግስት ፋጣንና ቀጣይነት ያለው የግብርና ልማት ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ ጥራት ያለው የግብዓት አቅርቦትና የኳራንቲን አገልግሎት ሥርዓት በመዘርጋት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ በማስፈለጉ የግብርና ምርታማነትን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጥቅም ላይ የሚውሉ የዕፅዋት ዘር፣ የእንሰሳት መኖ ዘር፣ የእንሰሳት መድሐኒት፣ ህያው ማዳበሪያ፣ የፀረ-ሰብል በሽታና ተባይ እንዲሁም አረም መከላከያ ኬሚካሎች እና ሌሎች የግብርና ግብአቶች በማምረት፣ በማከማቸት እና በማሰራጨት ሂደት የሚፈለገውን የጥራት ደረጃ ማሟላቱን ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በክልሉ ውስጥ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ እንዲሁም ከክልሉ ወደ ውጭ የሚወጡ ወይም ወደ ክልሉ የሚገቡ የሰብል በሽታና ተባይ እንዲሁም አረም እንዳይስፋፋ መከላከልና መቆጣጠር የሚያስችል የኳራንቲን አገልግሎት ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
ዋና ዋና ተግባራት
- በዕፅዋት ዘር ጥራት ማረጋገጥ
- የአፈር ማዳበሪያ ጥራት ማረጋገጥ
- የአግሮ ኬሚካል ጥራት ማረጋገጥ
- አነስተኛ የእርሻ መሳሪያ ጥራት ማረጋገጥ
- የዕፅዋት ኳራንቲን ኢንስፔክሽን ስራ
- ለግብርና ግብአት አምራቾች ህጋዊ ሰርተፍኬት (COC) መስጠት
- የዘር ጥራት ላብራቶሪ አገልግሎት
- በግልና በማህበረሰብ ተደራጅተው በዘር ብዜት ላይ ለሚሳተፉ አካላት ስልጠና መስጠት