ተልዕኮ እና ራዕይ
ተልዕኮ
በገጠርና በከተማ የሚኖረው ህብረተሰብ የአካባቢውን ሃብት መሰረት አድርጎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሩን ለመፍታት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ በተለያየ አይነትና ደረጃ የህብረት ስራ ማህበራትን በማጠናከርና በማደራጀት፣ አቅማቸውን በመገንባት፣ የግብይት ድርሻቸውን በማሳደግ፣ የመቆጠብ ባህልና መጠን በማሳደግ፣ የመበደር አቅም በመፍጠር፣ ህጋዊነታቸውንና ደህንነታቸውን በማስጠበቅ፣ የአባላትን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የህብረት ስራ ማህበራትን መፍጠር።
ራዕይ
በ2028 ዓ.ም የአባላትን ኑሮ መሻሻል በዘላቂነት ያረጋገጡ እና በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የላቀ ሚና ያላቸው የኅ/ሥራ ማህበራት ተፈጥረው ማየት።
የህብረት ስራ ማህበር ዓላማዎች
- 1. አባላት በግለሰብ ደረጃ ሊያሳሟቸው የማይችሏቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በጋራ ማሸነፍ፣ መቋቋምና መፍታት
- 2. የአባላትን እውቀት፣ ሀብትና ጉልበት በማስተባበር የተሻለ ውጤት ለማምጣት
- 3. በአባላት መካከል በራስ መተማመንን ማሳደግ
- 4. የምርት እና የአገልግሎት ወጪዎችን ለመቀነስ እና ለአባላት ግብዓቶችንና አገልግሎቶችን በዝቅተኛ ወጪ ለማቅረብ
- 5. የቴክኒክ እውቀትን በተግባር ላይ ለማዋል እና ሥራ ፈጣሪነትን ለማሳደግ
- 6. በአባላት መካከል የቁጠባ ባህልን ማዳበር እና ማሳደግ
- 7. ለአባላት ብድር መስጠትና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት
- 8. ለአባላት የሕይወት ኢንሹራንስ ሽፋን መስጠት
- 9. በእያንዳንዱ አባል ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና ኪሳራ ለመቀነስ መተባበር
- 10. የአባላትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም በትምህርትና በስልጠና ማዳበር
እሴቶች
የህብረት ስራ ማህበራት እሴቶች
- ራስን መርዳት
- በራስ መተማመን
- የዴሞክራሲ ባህል ማሳደግ
- እኩልነት
- ፍትሃዊነት
- አብሮነት
የሥነ ምግባር እሴቶች
- ሐቀኝነት
- ግልጽነት
- ተጠያቂነት
- ተሳትፎ
- ማህበራዊ ኃላፊነት
- ሌሎችን መንከባከብ
የህብረት ስራ ማህበራት ሚና
የህብረት ስራ ማህበራት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ወሳኝ ሚና ያበረክታሉ።