ሲዳማ · ኢትዮጵያ

የሰብል ጥበቃ ዳይሬክቶሬት

በልዩ ልዩ ተባዮች ምክንያት በምርትና ምርታማነት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ብክነት በመቀነስ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ከተመጽዋችነት ለመዳን የተቀመጠውን ሀገራዊና ክልላዊ ግብ ለማሳካት በሰብል ጥበቃ ዙሪያ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በመፈፀም ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ነዉ፡፡

የሰብል ጥበቃ ዳይሬክቶሬት
የሰብል ጥበቃ ዳይሬክቶሬት

ዓላማ ግብ

በልዩ ልዩ ተባዮች ምክንያት በምርትና ምርታማነት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ብክነት በመቀነስ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ከተመጽዋችነት ለመዳን የተቀመጠውን ሀገራዊና ክልላዊ ግብ ለማሳካት በሰብል ጥበቃ ዙሪያ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በመፈፀም ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ነዉ፡፡

የሰብል ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ተግባራትና ውጤቶች

  • በየበጀት ዓመቱ በፈጻሚዎች የሚታቀዱ ሥራዎች ከዳይሬክቶሬቱ ኃላፊነትና ተልዕኮ ጋር ተጣጥመው መዘጋጀታቸውን መከታተል፣ መፈፀማቸውን ማረጋገጥ፣ ለተፈፃሚነቱ ከፊዚካል ዕቅዱ ጋር ተመጣጣኝ በጀት እንዲፈቀድ ማድረግ፣ የሚዘጋጁ ዕቅዶች በክልላዊና በተቋማዊ ግቦች ላይ ተመስርተው እንዲዘጋጁ ማድረግ፤ ተግባራትን ለመፈፀም የሚችል በቂ የሰው ኃይል ተሟልቶ መገኘቱን ማረጋገጥ፤ የክትትል ሥርዓትን በማዘጋጀት ዳይሬክቶሬቱ የደረሰበትን የአፈፃጸም ደረጃ መገምገም፤ የግምገማ ውጤቱን በሥሩ ለሚገኙ ሠራተኞች በማሳወቅ አፈፃጸሙ የሚሻሻልበትን አስፈላጊ እርምጃ ይወስዳል፡፡
  • ዳይሬክቶሬቱ የሰብል ጥበቃ ሥራዎችን በማጠናከር በተባይ የሚደርሰውን የምርት ብክነትና ብክለት መቀነስና ማስወገድን ግብ በማድረግ የተቀረጹና የሚቀረጹ ፕሮጀክቶችን ለማስፈፀም የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ የሚገኝበትንም መንገድ ያፈላልጋል፤
  • በክልሉ ያለውን የሰብል ተባይ ክትትል፣ ቁጥጥርና የመከላከል ሥርዓትን ለማሻሻል ደንቦች፣ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች እንደአስፈላጊነቱ በመቅረጽ መነሻ ሀሳብ ያቀርባል፤ ዝግጅቱንም በመከታተል ያፀድቃል፤
  • ችግር ፈቺና የተቀናጀ የተባይ መከላከል ስልትን (IPM) መሠረት ባደረጉ የሥልጠና ርዕሶች ተከታታይ ሥልጠናዎች ተዘጋጅተው እንዲሰጡ እንዲሁም የሥልጠና ማንዋሎች እንዲዘጋጁ አቅጣጫ ይሰጣል፤ መፈፀማቸውንም ይከታተል፤
  • ከሰብል ጥበቃ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ጥራቱን የጠበቀና ጤናማ ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለመሆን በአርሶ አደሩና ከፊል አርብቶ አደሩ ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራትን ይቀይሳል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
  • የዕጽዋት ጥበቃ ክሊኒኮችን አቅም በመገንባት በተባይ ቅኝት፣ አሰሳ፣ መከላከልና ቁጥጥር ፈጣንና የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ እንዲደርሱ ተቀናጅቶ ይሰራል፡፡
  • ተባዮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ሎጀስቲክስ ተጠንተው መቅረባቸውን ይከታተላል፤ ለሚመለከተው አካልም ቀርቦ እንዲፀድቅ ያደርጋል፤
  • የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
  • ከዳይሬክቶሬቱ ጋር ግንኙነት ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያገናኙ የምክክር መድረኮች ማዘጋጀት፤ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የተባይ ልየታና መከላከል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራትን በበላይነት ማስተባበር፤ በዳይሬክቶሬቱ ከሚከናወኑ ተግባራት ጋር በተያያዘ በኃላፊነት ድርሻ፣ በትብብር ስምምነት፣ በድጋፍ ሰጪነት የተሰማሩ መንግስታዊ፣ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች ጋር በማቀናጀት፣ የልማት ድርጅቶችና፣ የሙያ ማህበራት ጋር ነባር ግንኙነቶችን አጠናክሮ ይቀጥላል፤ አዳዲስ ግንኙነቶችንም ይፈጥራል፤

የሥራው ባህሪ መግለጫዎችና ዉስብስብነት

  • ሥራው የዳይሬክቶሬቱን መምራት እና ማስተባበር ክልላዊ የሰብል ጥበቃ ሥራዎችን አፈጻጸም የሚያሻሽሉና ውጤታማነትን የሚያረጋግጡ ተግባራትን ማከናወን፤ ሰብል ጥበቃ ክሊኒኮችን አቅም በመገንባት ፈጣንና የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ማድረግ፤ የክትትል ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ፤ የአፈፃፀም ሪፖርቶች ወቅቱን ጠብቀው እንዲዘጋጁ በበላይነት ማስተባበርና አፈፃፀሙንም መከታተል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያገናኙ የምክክር መድረኮች ማዘጋጀት፤ በድንበር ዘለልነትና በወራሪነት የተፈረጁ ተባዮችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተከታታይ መግለጫ እና የተባይ ክስተትን የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች መስጠት ናቸው፡፡
  • በዓለም አቀፍ ደረጃ ተለዋዋጭ አየር ንብረት መከሰት፣ በተለዋዋጭ አየር ንብረት የሚመጡ አዳዲስ ተባዮች መከሰትና የአደገኛና ወራሪ እንዲሁም ኳራንቲን ተባዮች ዓይነትና መከሰቻ ያልታወቀ ሁኔታን ተከትለው የሚመጡ መሆናቸው፣ የአዳዲስ ተባዮች በዓይነትና በመከሰቻ ወቅት ተለይቶ መምጣት፤ አዳዲስ ዓለም አቀፍ ህግጋት መኖር፤ የአዳዲስ የምርት ተቀባይ አገራት ተጨማሪ ፍላጎት መጨመር በሥራ ሂደቱ በፈታኝነት የሚገለጹ ናቸው፡፡
  • እነዚህን ፈታኝ ሁኔታዎች በመፍታትና በማስወገድ ሥራውን ለማካሄድ ወሳኝ የሆኑ ግብአቶች እንዲሟሉ ተገቢውን የማሳመን ሥራ መሥራት፤ ሁኔታዎችን በመተንተንና በመተርጎም፣ ለፕሮጀክቶችም ተጨማሪ ደጋፊ አካላት የማፈላለግ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል፤ የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ግንኙነትና ቅንጅት፤ የፈፃሚና አስፈፃሚ ከፍተኛ ርብርብ እና ጥናት እንዲሁም ዘመናዊ ቤተ ሙከራ ፍተሻ መጠቀምን የሀገሪቱን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ህግጋት በማወቅና በማገናዘብ ቸግሩ ይፈታል፡፡